← All news
News Aug 20, 2026 · 19d ago

አሜሪካ ኢራንን ለማጥፋት «የአናኮንዳ ስትራቴጂ» እየተጠቀመች ነው ተባለ

በቴህራን የስልታዊ ጥናቶች ማዕከል ተንታኝ የሆኑት አሊ አክባር ዳሬይኒ፣ ትራምፕ እስካሁን ማሸነፍ ያልቻሉትን ጦርነት ለማጠናቀቅ «የአናኮንዳ ስትራቴጂን» እየተጠቀሙ መሆኑን ለአል ጃዚራ ተናግረዋል። “ይህ ስትራቴጂ ወታደራዊ ጥቃት ከመሰንዘሩ በፊት ጠላትን በኢኮኖሚ እና በፖለቲካ ለማነቅ ያለመ ነው” ሲሉ ዳሬይኒ ለአል ጃዚራ ተናግረዋል። “የአናኮንዳ እባብ በታደነው እንስሳ ላይ ተጠምጥሞ እንደሚያንቀው ሁሉ፣ አሜሪካ ባለፉት አምስት ወራት ያደረገችው ነገር ስለከሸፈ ይህንን ስትራቴጂ እየተከተለች ይገኛል ብለዋል።” ሆኖም ዳሬይኒ ኢራን ቀደም ሲል ማዕቀቦችን መቋቋም የቻለች መሆኗን በመግለፅ አሁንም እንደገና እንደምትቋቋመው ተከራክረዋል። “ትራምፕ ማሸነፍ በማይችሉት እና መውጣት በማይችሉበት ጦርነት ውስጥ ተዘፍቀዋል” ማለታቸውን አልጀዚራ ዘግቧል።