← All news
News Aug 18, 2026 · 20d ago

ግብጽ እና ኢትዮጵያን ለማደራደር‼️

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት የአረብ እና የአፍሪካ ጉዳዮች ከፍተኛ አማካሪ የሆኑት ማሳድ ቡሎስ ከሰሞኑ ግብፅን በጎበኙበት ወቅት 'ዶናልድ ትራምፕ በናይል ተፋሰስ ሀገራት መካከል የውሃ አጠቃቀምን በተመለከተ ስምምነት ላይ ለመድረስ እና በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ (GERD) ዙሪያ ያለውን አለመግባባት ለመፍታት፣ ካይሮ እና አዲስ አበባን እንደገና ለማደራደር ያላቸውን ዝግጁነት መግለጻቸውን አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።