← All news
News Aug 18, 2026 · 20d ago

የውጭ ሀገር ዜጎች የመኖሪያ ቤት ባለቤት የሚሆኑበት አሰራር ወደ ተግባር ገባ

የውጭ ሀገር ዜጎች የመኖሪያ ቤት ባለቤት እንዲሆኑ የሚፈቅደው አሰራር ወደ ተግባር መግባቱን የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር አስታውቋል። የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት በአዋጅ ቁጥር 1388/2017 መሰረት የውጭ ሀገር ዜጎች የመኖሪያ ቤት ባለቤት እንዲሆኑ የሚፈቅደውን አዋጅ ማጽደቁ ይታወሳል። በዚሁ መሰረት መመሪያ ተዘጋጅቶ ማንኛውም የውጭ ሀገር ዜጋ የመኖሪያ ቤት ባለቤት መሆን የሚያስችለው አሰራር ወደ ተግባር መግባቱ ነው የተገለጸው፡፡ በመመሪያው መሰረት አንድ የውጭ ዜጋ ቢያንስ 150 ሺህ ዶላር ካፒታል ሊኖረው እንደሚገባ ተመላክቷል። በተጨማሪም በመንግሥት ድጎማ የተገነቡ ቤቶችን መግዛት እንደማይችሉም ነው የተገለጸው።