6 ህገወጥ ኢትዮጵያውያንን በመኪና ሲያጓጉዝ የነበረው ሱዳናዊ 42 ሚሊዮን የኢትዮጵይ ብር እና የ15 ዓመት እስራት ሊቀጣ ነው::
በጃዛን ክልል 6 ኢትዮጵያውያንን በህገ-ወጥ መንገድ ሲያጓጉዝ የነበረ ሱዳናዊ በቁጥጥር ስር ዋለ በሳዑዲ አረቢያ የጃዛን ክልል የመጅሃዲን ጠቅላይ መመሪያ የጥበቃ አባላት የሀገሪቱን የድንበር ደህንነት ህግ በመጣስ በህገ-ወጥ መንገድ የገቡ 6 ኢትዮጵያውያንን በሲቪል መኪና ሲያጓጉዝ የነበረ አንድ የሱዳን ዜጋ በቁጥጥር ስር ማዋላቸውን አስታውቀዋል። የተያዘው አጓጓዥ ጉዳዩ በህግ እንዲታይ ለዐቃቤ ህግ የተላከ ሲሆን፤ ህገ-ወጥ የድንበር ጥሰት የፈፀሙት ኢትዮጵያውያንም አስፈላጊው የህግ ሂደት ከተፈፀመባቸው በኋላ ለሚመለከተው አካል ተልከዋል። የመጅሃዲን ጠቅላይ መመሪያ ቃል አቀባይ እንዳስገነዘቡት፤ የድንበር ደህንነት ህግ ተጣሾች ወደ ሳዑዲ አረቢያ እንዲገቡ * ማመቻቸት፣ * ማጓጓዝ፣ * መጠለያ መስጠት ወይም ማንኛውንም አይነት የትብብር ድጋፍ ማድረግ በህግ ያስጠይቃል። በዚህ የወንጀል ድርጊት ላይ የተሰማሩ አካላት ላይ የሚከተሉት ከባድ ቅጣቶች ይጣላሉ፦ 1. እስከ 1 ሚሊዮን የሳዑዲ ሪያል (በወቅቱ የምንዛሬ ተመን ከ42 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ብር የሚደርስ የገንዘብ መቀጮ)። 2. እስከ 15 ዓመት የሚደርስ ፅኑ እስራት። 3. በህገ-ወጥ ዝውውሩ ወቅት ጥቅም ላይ የዋለው የትራንስፖርት ተሽከርካሪ ሙሉ በሙሉ ይወረሳል። አስፈላጊውን ህጋዊ የጉዞ ሰነድ ሳይይዙ የሚደረግ የድንበር ጥሰትና ህገ-ወጥ ዝውውር ለከባድ የእስራትና የገንዘብ ቅጣት የሚዳርግ በመሆኑ ዜጎች ጥንቃቄ እንዲያደርጉ መልእክት ተ አስተላልፏል። Via Saudi Gazette