ከ3 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጣ አረቄ ተደፋ
በምዕራብ ኦሞ ዞን ቤሮ ወረዳ ለወንጀል መንስኤ የሆነና ከ3 ሚሊዮን ብር በላይ የዋጋ ግምት ያለው ህገ-ወጥ የሀበሻ አረቄ በቁጥጥር ስር ውሎ እንዲደፋ ተደረገ። የወረዳው ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ክፍል ኃላፊ ሳጅን ጌታሁን ክፍሌ እንደገለጹት፤ ህገ-ወጥ አረቄ ማዘጋጀትና ማሰራጨት ለጤና ጉዳትና ለወንጀል መበራከት መንስኤ በመሆኑ ቁጥጥሩ ተጠናክሮ ይቀጥላል። ህብረተሰቡም ጥቆማ በመስጠት ከጸጥታ አካላት ጋር እንዲተባበር ጥሪ አቅርበዋል። መረጃው የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ነው።