← All news
News Aug 17, 2026 · 21d ago

ሰበር

አቶ ክርስቲያን ታደለ የመንግሥትን የምሕረት ቅድመ ሁኔታ ተቀበሉ! ከአማራ ክልል ቀውስ ጋር በተያያዘ በሽብር ተከስሰው በእስር ላይ የሚገኙ በርከት ያሉ ታሳሪዎች መንግሥት ያቀረበላቸውን በቅድመ ሁኔታ የታሠረ የምኅረት መጠየቂያ ሠነድ መፈረማቸውን ዋዜማ ራድዮ ዘግቧል፡፡ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባሉ ክርሰቲያን ታደለን፣ ረዳት ፕሮፌሰር ማዕረጉ ቢያበይንን ጨምሮ በርካታ እስረኞች የምኅረት መጠየቂያውን በመሙላት ስምምነታቸውን እንደገለጡ ምንጮች እንደነገሩት ዘገባው ጠቅሷል። አምስት ጋዜጠኞችንና ፖለቲከኞችን ጨምሮ 30 ያህል እስረኞች ግን ሠነዱን 'አንፈርምም' ማለታቸው ታውቋል። ሠነዱን አንፈርምም ካሉት መካከል፤ የአማራ ክልል ምክር አባሉ ዮሐንስ ቧያለው፤ ዶ/ር ሲሳይ አውግቸው፣ ዶ/ር ወንደወሠን አሠፋ፣ መስከረም አበራ እና ጎበዜ ሲሳይ ይገኙበታል ተብሏል። የምኅረት ሠነዱን እንዲፈርሙ የቀረበላቸው እስረኞች 300 ገደማ እንደሚጠጉ ታውቋል፡፡