← All news
News Aug 17, 2026 · 22d ago

በጥቃቱ የተሳተፉ ተጠርጣሪዎች በአዲስ አበባ ፖሊስ ቁጥጥር ስር ዋሉ!

በማህበራዊ ሚዲያ ገፆች ሲሰራጭ በነበረው አሳዛኝ የጥቃት ቪዲዮ ውስጥ ተሳትፋለች የተባለችው “ፈርደውስ” እና አባሪዎቿ፣ በአዲስ አበባ ፖሊስ ፈጣንና የተቀናጀ ኦፕሬሽን በህግ ጥላ ስር እንዲውሉ ተደርገዋል። ህብረተሰቡ መረጃዎችን ለህግ አካላት ብቻ እንዲያደርስ ቀደም ሲል የቀረበውን ጥሪ ተከትሎ፣ የህግ አስከባሪዎቻችን የተጣለባቸውን ኃላፊነት በከፍተኛ ሙያዊ ብቃት በመወጣት እውነታውን አጣርተው ተጠርጣሪዎቹን በቁጥጥር ስር አውለዋል። የህዝብን ሰላምና ደህንነት ለማስከበር፣ ጥፋተኞችን ለፍትህ ለማቅረብ እና የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ የአዲስ አበባ ፖሊስ ላሳየው ፈጣን ምላሽ ከፍተኛ ምስጋና እየቀረበለት ይገኛል፡፡