ጨረቃና ፀሐይ ተጋጥመው በፈጠሩት ጨለማ ውስጥ አስደናቂ የስኬትቦርድ ትዕይንት ተከናወነ
የስፔኑ ስኬትቦርደር እና ብሎገር ዳኒ ሊዮን ሙሉ የፀሐይ ግርዶሽ በታየበት ቅጽበት የማይታመን እና አስደናቂ ትዕይንት በመስራት ዓለምን ጉድ አሰኝቷል። ፀሐይ በጨረቃ ተጋርዳ በሰማይ ላይ የሚያብረቀርቅ የብርሃን ቀለበት በተፈጠረበት ቅፅበት፣ ዳኒ ሊዮን በስኬትቦርዱ ያሳየው የተለየ ክህሎት እና የተ የተቀረጸው ድንቅ ቪዲዮ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ትልቅ መነጋገርያ ሆኗል። ይህ ድንቅ ትዕይንት በተቀረጸ በጥቂት ሰዓታት ውስጥ ብቻ ከ40 ሚሊዮን በላይ እይታዎችን በማስመዝገብ በበይነመረብ ላይ በከፍተኛ ሁኔታ ተሰራጭቷል። የተፈጥሮን ብርቅዬ ክስተት ከስፖርታዊ ክህሎት ጋር በማቀናጀት የቀረበው ይህ ትዕይንት፣ የብዙዎችን ቀልብ የሳበና የዓመቱ ምርጥ ቪዲዮ ተብሎ በብዙዎች ዘንድ ተወድሷል።