← All news
News Aug 15, 2026 · 24d ago

ሆርሙዝ የአሜሪካ ግዛት ሊሆን❓‼️

የሆርሙዝ ሰርጥ በቅርቡ የአሜሪካ ግዛት  ይሆናል - ትራምፕ‼️ የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በቅርቡ የሆርሙዝ ሰርጥ የአሜሪካ ግዛት መሆኑን እንደሚያወጂ አርብ ዕለት አስታወቁ።  ትራምፕ በኒውዮርክ ጋርደን ሲቲ በሚገኘው አዲሱ ናሳው ካውንቲ ፖሊስ አካዳሚ ባደረጉት ንግግር «በጣም በከባድ ሁኔታ እየተሸነፈች ያለችውን ኢራንን ድል እያደረግን እንገኛለን፣ በቅርቡ የሆርሙዝ ሰርጥ የአሜሪካ ግዛት እንደሆነ አውጃለሁ» ብለዋል። ትራምፕ አክለውም አሜሪካ በስትራቴጂካዊው የውኃ መስመር ላይ የጣለችው እገዳ መቀጠሉን በመጥቀስ «እኛ ካልፈለግን በስተቀር ምንም ዓይነት መርከብ ማለፍ አይችልም» ሲሉ ተናግረዋል። ሆኖም የኢራን ወታደራዊ ባለሥልጣናት አሜሪካ ሰርጡን አየተቆጣጠረች ነው መባሉን አስተባብለዋል።  የኢራን ማዕከላዊ ወታደራዊ ዕዝ ሐሙስ ዕለት በሰጠው መግለጫ የአሜሪካን አስታያየት «መሠረት የሌለው ሐሰትና ፈጠራ» ሲል ጠርቶታል።