← All news
News Aug 15, 2026 · 24d ago

ሰበር ዜና

ሀገሬ ቴሌቪዥን የ2026/27 የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግን በነፃ ሊያስተላልፍ ነው ። ሀገሬ ቴሌቪዥን የ2026/27 የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የነጻ የአየር ስርጭት (FTA) ብቸኛ ባለመብት በኢትዮጵያ መሆኑን አስታውቋል ። ከዚህ ቀደም ኢቲቪ በሳምንት አንድ ጨዋታ ሲያስተላልፍ እንደነበር ይታወቃል አሁን ሀገሬ ቴሌቪዥን ዝርዝር መረጃ ባይገልጽም ጨዋታዎቹን ለማስተላለፍ ፍቃድ ማግኘቱን በይፋ አስታውቋል። ከወር በፊት የ2026 የተመረጡ 34 የዓለም ዋንጫ ጭዋታዎችን ከሀገራችን ውስጥ ካሉ ቴሌቪዥን ጣብያዎች  በብቸኝነት የዓለም ዋንጫ ጭዋታዎችን ማስተላለፉ አይዘነጋም ።