ከጥርስ ቡርሽ እስከ ማንችስተር ሲቲ! የያቡ አርትስ አስደናቂ ድል
በጥርስ ቡርሽ ታዋቂ ተጫዋቾችን በመሳል የሚታወቀው ኢትዮጵያዊው ወጣት ባለጥበብ ያብ አርትስ (Yabu Arts)፣ የማንችስተር ሲቲውን ክንፍ ጀርሚ ዶኩን በልዩ ጥበብ ስሎ አቅርቧል። ከ60 ሚሊዮን በላይ ተከታይ ያለው የማንችስተር ሲቲ ኦፊሴላዊ የፌስቡክ ገፅም በስራው በመደመም ቪዲዮውን በገፁ ላይ አጋርቶታል። ይህ ድንቅ ስራ የአለም አቀፍ እውቅናን ያተረፈ ሲሆን ለኢትዮጵያዊው ወጣት ትልቅ ኩራት ሆኗል።