በሱዳን ድንበር ከባድ ውጊያ‼️
በቅርቡ በሱዳን ጦር ቁጥጥር ስር የነበረችው ኩርሙክ በRSF(ፈጥኖ ደራሽ) እጅ ገባች። በሱዳን ጦር (SAF) እና በፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ (RSF) መካከል ባለው ከባድ ውጊያ፣ ስትራቴጂካዊቷ የድንበር ከተማ ኩርሙክ በRSF እጅ ገብታለች። ዋና ዋና መረጃዎች፦ 👉 በውጊያው በርካታ የሕወሓት ታጣቂዎች መማረካቸው ተገልጿል። 👉 የሱዳን ጦር ከተማዋን የለቀቀው ከኢትዮጵያ በኩል በድሮን እና በከባድ መሳሪያ ለ3 ቀናት ድብደባ በመፈፀሙ ነው ብሏል (ሱዳን ትሪቡን)። 👉 ከኤድ ዳማዚን 136 ኪ.ሜ የምትርቀው ኩርሙክ፣ ቁልፍ የድንበር ማቋረጫና የወታደራዊ አቅርቦት መስመር ናት።