← All news
News Aug 14, 2026 · 25d ago

አባቴ... አሁንም ከእኛ መለየትህን ማመን አልቻልኩም"

The Goat ሊዮኔል ሜሲ ለአባቱ ለጆርጅ ሜሲ የጻፈው ልብ የሚነካ የመሰናበቻ ደብዳቤ አባቴ ከእንግዲህ አይንህን የማላየው፣ ከእኔ ጋር የማትነጋገር መሆኑን መቀበል ከብዶኛል። የምትሰቃይ እንደነበር እና አሁን ማረፍህ የተሻለ መሆኑን ባውቅም፣ ግን በጣም ፈጥነህ ተለየኸን። ገና አብረን የምናሳልፈውና የምንደሰትበት ብዙ ነገር ነበረን። በመጨረሻው የዓለም ዋንጫ እንድጫወት ሁልጊዜ ትነግረኝ ነበር፤ ውድድሩ ከመጀመሩ ጥቂት ቀናት በፊት ግን ጤናህ እየታወከ መጣ። በውድድር ላይ ሳለሁ የማትገኝበት የመጀመሪያው ጊዜ ነበር፤ ነገር ግን እናቴ ደህና እንደምትሆን እና ለመጓዝ እንደምትችል ነግራኝ ነበር። ወደ ፍፃሜው እንደምንደርስና መጥተህ ጨዋታውን እንደምትመለከት ነግሬህ ነበር። ስለተፈጠረው ነገር ሁሉ ማውራት ስላልቻልኩ ወደ አንተ መጣሁ። ምንም ነገር መደሰት አልቻልክምና። ሻምፒዮን ባንሆንም እያንዳንዱን ጨዋታ እንዴት እንደተደሰትንበት በፍጹም አላወቅክም። አሁንም ቢሆን አንተ ልክ ነበርክ፤ በዚያ መገኘት እና መጫወት ነበረብህ። ይህንን የምነግርህ ልናወራው ያልቻልነው ብቸኛው ነገር ስለሆነ ነው፤ ምክንያቱም ሌላውን ነገር ሁሉ አስቀድመህ ታውቀዋለህ። በየቀኑ እናወራ ነበር፣ በእኔ ፕሮግራሞች ምክንያትም በቻልንበት ጊዜ ሁሉ እንገናኝ ነበር። ያለ አንተ ምን እንደማደርግ አላውቅም፣ እንዴትስ ለመቀጠል እንደምችል አላውቅም። እኔ እግር ኳስ ብቻ ነው የምጫወተው፣ አሁን ግን ለረጅም ጊዜ መጫወቴን እቀጥላለሁ ወይ የሚል ብዙ ጥርጣሬ አደረብኝ። ከጅምሩ ጀምሮ ከጎኔ ነበርክ፣ እስከ መጨረሻውም በጣም ቅርብ ነበርክ። ለምን ጥቂት ጊዜ ታግሰህ አብረን አልጨረስንም? ደስታህ ቤተሰብህን፣ ባለቤትህን፣ ልጆችህን ማየት እንደሆነ አውቃለሁ፤ ከሁሉም በላይ ደግሞ ሌሎች ሳይረዱ እኔ ስጫወት ማየት እንደነበር አውቃለሁ... ከትንሽነቴ ጀምሮ ሁልጊዜ እንደዚያ ነበር። ከስራ እንደተመለስክ ወደ ልምምድ ቦታ ሁሉ ትወስደኝ ነበር። በእርግጥም አንዱንም ጨዋታ አታልፍም ነበር። እኔን ስትመለከት እንዴት ትጨነቅ እንደነበር እና እንዴት ትዝናናበት እንደነበር አስታውሳለሁ:: አባት፣ ጓደኛ እና ወኪሌ ነበርክ። በየወቅቱ መሆን ያለብህን ሰው ሁልጊዜ ነበርክ፤ በፍጹም አልተሳሳትክም። ከአንዳንድ ቅርታዎች ወይም ጭቅጭቆች ባሻገር ሁልጊዜ ልክ ነበርክ። በመጨረሻም ሁሉም ነገር አንተ ባልከው ይደመደማል። በጣም እናፍቅሃለሁ፣ ነገር ግን ሁልጊዜ በልቤ ውስጥ ትኖራለህ፤ በተለይም በልጆቼ አስተዳደግ ውስጥ፣ ምክንያቱም አንተ እኔን ባደገከኝ እና ባስተማርከኝ መንገድ ነው ልጆቼን የምኮተታቸው እና የማደግደው። በሰላም እረፍ፣ እዚህ እንዳደረግከው ሁሉ ከላይ ሆነህ ጠብቀን። ስለ ሁሉም ነገር አመሰግናለሁ። እወድሃለሁ አባቴ! ❤️"