በ2019 በጀት ዓመት 13.4 ቢሊዮን ዶላር ለማግኘት ታቅዶ እየተሠራ ነው ተባለ
በ2019 በጀት ዓመት 13.4 ቢሊዮን ዶላር ለማግኘት ታቅዶ እየተሠራ ነው ተባለ ኢትዮጵያ በተጠናቀቀው የ2018 በጀት ዓመት ከወጪ ንግድ ከ11.2 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር በላይ ገቢ ማግኘት መቻሏን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ። ይህም ከአጠቃላይ ዕቅዱ የ119 በመቶ በላይ አፈጻጸም የተመዘገበበት መሆኑ ተገልጿል። የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትሩ ዶክተር ካሳሁን ጎፌ ከወጪ ምርት ላኪዎች ጋር ባካሄዱት የምክክር መድረክ እንደገለጹት፤ የተመዘገበው ከፍተኛ ውጤት ሀገራዊ የማክሮ-ኢኮኖሚ መረጋጋትን ለማምጣት ትልቅ አስተዋጽኦ አበርክቷል። በቀጣዩ የ2019 በጀት ዓመት ደግሞ የሀገሪቱን የውጭ ምንዛሬ ገቢ ይበልጥ ለማሳደግ 13.4 ቢሊዮን ዶላር ለማግኘት ታቅዶ ወደ ሥራ መገባቱን ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በማህበራዊ ትስስር ገጹ ባጋራው መረጃ አሳውቋል። ይህንን ዕቅድ ለማሳካት በሥራ ሂደት የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችን በጋራ ለመፍታትና ላኪዎችን በቁርጠኝነት ለመደገፍ ከስምምነት መደረሱም ተገልጿል።