← All news
News Aug 11, 2026 · 28d ago

በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በኢቦላ ወረርሽኝ ምክንያት የሟቾች ቁጥር 2,000 አለፈ።

በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የተከሰተው እና በታሪክ እጅግ ፈጣኑ ተብሎ የተገለጸው የኢቦላ ወረርሽኝ የሟቾች ቁጥር 2,000 ማለፉን የሀገሪቱ የጤና ባለስልጣናት አስታውቀዋል። ቁጥራዊ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት እስካሁን ድረስ ፦ ⚫ በአጠቃላይ 4,381 የተረጋገጠ የኢቦላ ተጠቂዎች ተመዝግበዋል፤ ⚫ 2,011 ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል። ⚫ 704 ታካሚዎች በተለዩ የህክምና ማዕከላት ውስጥ ህክምና እየተደረገላቸው ይገኛል። ወረርሽኙ ከተከሰተ በኋላ የመጀመሪያዎቹን 1,000 ሰዎች ለመግደል ዘጠኝ ሳምንታት ያህል የፈጀበት ቢሆንም፣ ሁለተኛውን 1,000 ሰዎች ለመግደል ግን የወሰደበት ጊዜ ሶስት ሳምንታት ብቻ ሆኖ ተመዝግቧል። ይህ ወረርሽኝ እ.ኤ.አ. ከ2014 እስከ 2016 በምዕራብ አፍሪካ ከተከሰተው እና ከ11,000 በላይ ሰዎችን ከገደለው ወረርሽኝ ቀጥሎ በታሪክ ሁለተኛው ትልቁ የኢቦላ ወረርሽኝ ሆኗል። በኢቱሪ ግዛት እና አካባቢው ባለው የታጠቁ አማፂያን ግጭት እንዲሁም የመሰረተ ልማት አለመሟላት ምክንያት የመከላከል ሥራው አስቸጋሪ እንዳደረገው ሲገለጽ የቆየ ሲሆን፥ አሁን ደግሞ የጤና ባለሞያዎች ከክፍያ ጋር በተያያዘ የሚያሰሟቸው ቅሬታዎችና አድማዎች ሌላ ፈተና ደቅነዋል ተብሏል።