← All news
News Aug 10, 2026 · 28d ago

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ በጉራጌ ዞን አበሽጌ ወረዳ የተፈፀመ‼️

ተመስገን ጌታቸው፣ ይታገሱ አሰግደው እና ግዛው ግርማዬ የተባሉ ሶስት ግልሰቦች ከተሳፈሩበት የሕዝብ ማጓጓዣ መኪና ላይ “ፋኖ ናችሁ” በሚል ውንጀላ ተገደው እንዲወርዱ ከተደረጉ በኋላ መገደላቸውን የአካባቢው ምንጮች ለመሠረት ሚድያ ተናግረዋል። ድርጊቱ የተፈጸመው አገና በተባለችው ልዩ ቦታ ሲሆን ወንጀሉን የፈጸሙት የመንግስት ኃይሎች ከአካባቢው የአበሽጌ አገና ፖሊስ እና ሚሊሻ አባላት ጋር በመተባበር እንደሆነ ተጠቅሷል። ግለሰቦቹ የተለያዩ ወንጀሎችን እንደፈፀሙና የተያዙትም ከአካባቢው ለማምለጥ በሚሞክሩበት ጊዜ መሆኑንና ከተያዙ በኋላ እንዲረሸኑ መደረጉን የአካባቢው ምንጮች ይገልፃሉ። Via:- መሰረት ሚዲያ