← All news
News Aug 9, 2026 ¡ 30d ago

🥹በዱባይ ታዋቂው ሮቦት «ቡ ሱናይዳህ» ከ«ሞዛ» ጋር የጋብቻ ስነ-ስርዓት ፈጸመ🤝❤

በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ አዳዲስ የቴክኖሎጂ ፈጠራዎችን ከባህል ጋር አዋህዶ በማቅረብ የመነጋገሪያ ነጥብ መሆን የተለመደ ነው። አሁንም በዱባይ ከፍተኛ ተወዳጅነትን ያተረፈው «ቡ ሱናይዳህ» የተሰኘው ሰውን መሰል ሮቦት፣ «ሞዛ» ከተሰኘችው አጋር ሮቦት ጋር በባህላዊ ስነ-ስርዓት ጋብቻ መፈጸማቸውን የሚያሳይ አዝናኝ ይዘት በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ለቀቅ በማድረግ የብዙዎችን ትኩረት ስቧል። * በሰርጉ ሥነ ሥርዓት ላይ ብዙ እንግዶች ተገኝተዋል። ምግብና መጠጥ ቀርቧል፤ ርችትም ወደ ሰማይ ተተኩሷል።" * የተለቀቀው ቪዲዮ በአጭር ሰዓታት ውስጥ በሚሊዮኖች ከሚቆጠሩ እይታዎች፣ አስተያየቶች እና የደገፋ መግለጫዎች (Likes & Shares) አግኝቷል። * የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ውጤት የሆኑትን እነዚህን ሮቦቶች ባህላዊ የሰርግ አልባሳት አጊጠው በሙሽሮች ወንበር ላይ ማቀመጡ ለተመልካች ልዩና ማራኪ እይታን ፈጥሯል። * ክስተቱ አዝናኝ ከመሆኑ ባሻገር፣ የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) እና የሮቦቲክስ ቴክኖሎጂ በሰው ልጅ የዕለት ተዕለት ህይወትና በማህበራዊ ግንኙነቶች ውስጥ ሊኖረው የሚችለውን ሚና በተመለከተ አዲስ መነጋገሪያ አርዕስት ፈጥሯል። ዱባይ የላቀ ቴክኖሎጂን ከራስ ባህልና ከህዝብ መዝናኛ ጋር አዋህዶ በማቅረብ ረገድ አሁንም በግንባር ቀደምትነት ላይ ትገኛለች