← All news
News Aug 7, 2026 · 32d ago

የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር አዘዘው ጫኔ  በተደራጀ የኢኮኖሚ ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ከዋሉት 91 ግለሰቦች መሀል ይገኙበታል ተባለ

​በጉዳዩ ላይ ከተካሄደው ምርመራ ከተገኙ ግኝቶች መካከል፡- 👉​በገቢዎች እና ጉምሩክ አስተዳደር ውስጥ የተደራጀ ህገ-ወጥ መረብ መኖሩ ተጠቁሟል። 👉​የታክስ ምዘናዎችን ማሻሻጥ፣ ሀሰተኛ ደረሰኞችን ማስተናገድ እና የኤሌክትሮኒክስ መረጃዎችን መሰረዝ እንደ ዘዴ ጥቅም ላይ ውለዋል ተብሏል። 👉​ድርጊቶቹ የመንግስት ገቢ እንዲቀንስ ማድረጋቸው ተመልክቷል። ​በአሁኑ ወቅት ጉዳዩ በህግ አስከባሪ አካላት ተይዞ ምርመራው በዝርዝር እየተካሄደ ይገኛል።