← All news
News Aug 6, 2026 · 32d ago

የመሳሪያ ዲፖ ተያዘ‼️

በሱዳን የሚንቀሳቀሰው የህወሓት አርሚ 70 በሸረሪና ግንባር አከማችቶት የነበረው የመሳሪያ ዲፖ ተያዘ‼️ ከሸረሪና ካምፕ ወጣ ብሎ 'ግዴማ' በተባለች ቦታ መጋዘን ውስጥ እንዲሁም ከመሬት በታች በኮንክሪት በተሰራ ግዙፍ ምሽግ ተጠራቅሞ የነበረ ተተኳሽ፣ የቡድንና የነፍስ ወከፍ መሳሪያ፣ ሮኬት፣ የአጭር እና መካከለኛ ርቀት ሚሳይሎች፣ RPG-7፣ የሳተላይት ስልኮች፣ የሬዲዮ መገናኛ፣ የቅኝት ድሮኖች፣ የመኪና መለዋወጫዎች እና ለጊዜው ምንነታቸውን ለመለየት ያልተቻሉ የጦር መሳሪያዎች ገቢ መደረጋቸውን ምንጮቹ አረጋግጠዋል። እንደ ወታደራዊ ምንጮቹ ገለፃ ከሆነ፤ በትናንትናው እለት ብቻ ከሸረሪና እና ግዴማ ካምፕ 31 ከባድ ተሳቢ ተሽከርካሪዎች ከአርሚ 70 የተማረኩ የተለያዩ ትጥቆችን ወደ ሁመራ እና ዳንሻ ከተማ ተጓጉዘዋል። ለዚህ ዲፖ መገኘት የተማረኩ የአርሚ 70 ታጣቂዎች አስተዋጽኦ አድርገዋል።