← All news
News Aug 6, 2026 · 33d ago

አውሮፓ በእሳት እየተቃጠለች ነው‼

በአውሮፓ የሙቀት መጠኖች አዲስ ሪኮርድ እያሰመዘገቡ ነው፣ ሰደድ እሳቶች እየተስፋፉ ነው፣ የኒውክሌር ኃይል ማመንጫዎች ምርታቸውን እየቀነሱ ነው ​እጅግ በጣም ሞቃታማ እና ደረቅ የሆነው የበጋ ወቅት በግብርና ላይ ከባድ ጉዳት እያደረሰ ይገኛል አዲስ የሙቀት ሪኮርድ፦ በአውሮፓ የሙቀት መጠኑ በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሮ በኦስትሪያ እስከ 41.2°C ተመዝግቧል። ​የኃይል ማመንጫዎች አቅም መቀነስ፦ የዳኑብ እና የሳቫ ወንዞች የውሃ መጠን በመቀነሱ በሃንጋሪ እና በስሎቬንያ የሚገኙ የኒውክሌር ኃይል ማመንጫዎች ምርታቸውን ለመቀነስ ተገደዋል። ​የደን እሳት እና መፈናቀል፦ በፈረንሳይ፣ እስፓንያ፣ አልባንያ እና ግሪክ አጥፊ የእሳት አደጋዎች የተከሰቱ ሲሆን በሺዎች የሚቆጠሩ ሄክታር መሬቶች ተቃጥለው በርካቶች ተፈናቅለዋል። ​የኢኮኖሚና የግብርና ጉዳት፦ በራይን ወንዝ የውሃ ማነስ ምክንያት የመርከብ ትራፊክ ሲስተጓጎል፣ በታላቋ ብሪታንያ ደግሞ እ.ኤ.አ. ከ1984 ወዲህ እጅግ አነስተኛው የእህል ምርት እንደሚመዘገብ ተገምቷል። ​የሕይወት እልቂት፦ በሙቀት ማዕበሉ ምክንያት በአህጉሩ ከ1,300 በላይ ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል።