← All news
News Aug 5, 2026 · 34d ago

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ረጅም ርቀት መጓዝ የሚችሉ አውሮፕላኖች ግዢ እየተከናወነ ነው

አየር መንገዱ ወደ አውስትራሊያ በረራ የመጀመር ከፍተኛ ፍላጎት እንዳለውና ገበያውም እንዳለ መረዳቱን የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው ተናግረዋል። ነገር ግን አሁን ላይ ወደ አውስትራልያ በረራ ለመጀመር " አውሮፕላን የለንም " ብለዋል። ለዚህም ረጅም ርቀት መጓዝ የሚችሉ አዳዲስ አውሮፕላኖች ግዢ እየተከናወነ መሆኑን ተጠቁሟል። አየር መንገዱ ከጥር 2020 ዓ.ም ጀምሮ ከቦይንግ እና ኤርባስ ኩባንያዎች የሚረከባቸው በርከት ያሉ አዳዲስ አውሮፕላኖች በመኖራቸው ለአውስትራሊያው መስመር በረራ መጀመር ዝግጅት እንደሚደረግ ገልጸዋል።