የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ።
በአማራ ክልል የ2018 የትምህርት ዘመን የ8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና ውጤት ይፋ ሆኗል።ከሰኔ 3-5/2018 ዓ.ም የተሰጠውን የ8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና 173,699 ተማሪዎች ውስደው ነበር። ፈተናውን ከወሰዱት ተማሪዎች መካከልም 135,003 (77.72%) ተማሪዎች 50% እና በላይ ውጤት አስመዝግበዋል። ተማሪዎችም ውጤታቸውን https://amhara.ministry.et/#/result የሚለውን አድራሻ በመፃፍ ፤ በሚመጣው ቅጽ ላይ የተማሪ መለያ ቁጥር (Registration Number) እና ስም በአማርኛ በማስገባት ፤ ዉጤት ይመልከቱ (Check your result) የሚለውን ቁልፍ በመጫን ማየት ይችላሉ፡፡ በተጨማሪም @emacs_ministry_result_qmt_bot ላይ መመልከት ይችላሉ። ተማሪዎች ማንኛውም ከውጤት ጋር የተያያዘ ቅሬታ ካላቸው https://amhara.ministry.et/#/complaint ላይ በመግባት ቅሬታቸው ማቅረብ እንደሚችሉ የክልሉ ትምህርት ቢሮ አሳውቋል። 2018 ዓ.ም የ6ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና ውጤት ነገ ይፋ ይደረጋል ተብሏል።