ለጥገና ሥራ የሚቋረጥ የኃይል አቅርቦት
ነገ ሐምሌ 26 ቀን 2018 ዓ.ም የጥገና ሥራ ለማከናዎን የኃይል አቅርቦት የሚቋረጥባቸው አካባቢዎች፦ ✅ ከጠዋቱ 2፡30-8፡30 👉 ቱሉዲምቱ ኮንዶሚኒየም፣ ዓለም ባንክ 700 ማህበራት ቤቶች፣ ገላን እና አካባቢው፣ ✅ ከጠዋቱ 12፡00 - 4፡00 👉 በመቀሌ ቀበሌ 14፣ 15 ፣ 17 ፣ መቀሌ ተክላይማኖት እና አካባቢው፣ ✅ ከጠዋቱ 2፡30-10፡00 👉 አዋሽ መልካሳ እና አከባቢው፣ ✅ ከጠዋቱ 3፡00-7፡00 👉 በበህዳር ሪጅን አዲስ ዓለም፣ ኦቪድ ኮኒስትረክሽን፣ ሰማታት፣ ግዮን ት/ቤት፣ ሚሊኒየም ት/ቤት፣ ናይል ቪው ሆቴል እና አካባቢው የኃይል አቅርቦት ተቋርጦ ይቆያል፡፡ ስለሆነም በተጠቀሱት አካባቢዎች የምትገኙ ክቡራን ደንበኞቻችን የጥገና ሥራው ተጠናቆ የኃይል አቅርቦቱ እስኪ መለስ ድረስ በትዕግስት እንድትጠብቁን በትህትና እንጠይቃለን። #የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት