አሊኮ ዳንጎቴ ከሃብታቸው ሲሶውን ለበጎ አድራጎት ድርጅት ሊያውሉት ነው።
የአፍሪካ ቁጥር አንድ ባለሀብት የሆኑት ናይጄሪያዊው ቢሊየነር አሊኮ ዳንጎቴ፣ ከሀብታቸው ውስጥ አንድ ሦስተኛውን (35 ቢሊዮን ዶላር የሚደርስ) ኃብታቸውን ለበጎ አድራጎት ሥራዎች ሊለግሱ መሆኑ ተገልጿል። ልጃቸው ፋጢማ ዳንጎቴ በቅርቡ ከብሉምበርግ ጋር በነበራት ቃለ-መጠይቅ ድጋፉን በስማቸው በተቋቋመው ፋውንዴሽን በኩል ለበጎ አድራጎት ሥራዎች እንደሚያውሉት ይፋ አድርጋለች።