← All news
News Jul 31, 2026 · 39d ago

አፈሳና ጦርነት የሰጉ የትግራይ ተማሪዎች አሁንም "ግቢ" ናቸው!

አስገዳጅ ወታደራዊ ምልመላን በመስጋት ወደትግራይ ክልል መመለስ ያልቻሉ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ክረምቱን በግቢው ውስጥ ለማሳለፍ ፍቃድ ማግኘታቸውን ዋዜማ ሰምታለች፡፡ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩ የትግራይ ተወላጅ ተማሪዎች፣ በትግራይ ክልል ባለው ወቅታዊ ሁኔታ እና አስገዳጅ ወታደራዊ ምልመላ ስጋት ምክንያት ወደ ክልላቸው መመለስ ባለመቻላቸው፤ ክረምቱን በዩኒቨርሲቲው ውስጥ እንዲያሳልፉ ተፈቅዶላቸዋል። ዋዜማ ያነጋገረቻቸው ተማሪዎች እንደገለጹት፤ ጥያቄው መጀመሪያ ላይ በዩኒቨርሲቲው በኩል ተቀባይነት አጥቶ ለሳምንታት የቆየ ቢሆንም፤ ከጊዜያት በኋላ ግን በትምህርት ሚኒስቴር ውሳኔ መፍትሔ ሊያገኝ ችሏል።