← All news
News Jul 31, 2026 · 39d ago

የ6ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ!!

​በኦሮሚያ ክልል የ1ኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ የ6ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ሰኔ 08 - 09/2018 ዓ.ም ተሰጥቶ የነበረ ሲሆን፣ ዛሬ የተማሪዎች ውጤት ይፋ ሆኗል። ​👉 የማለፊያ ነጥብ 50% እና ከዚያ በላይ እንዲሆን ተወስኗል። ​👉 ፈተናውን ከተቀመጡ 517,209 ተማሪዎች ውስጥ የማለፊያ ነጥብ (50% እና ከዚያ በላይ) በማስመዝገብ ወደ ሚቀጥለው ክፍል የተሸጋገሩት 464,839 (89.9%) ተማሪዎች መሆናቸው ታውቋል። ​ከተፈተኑት ተማሪዎች መካከል፡ 📍 ወንድ 267,307 ውስጥ 91.2% እና 📍 ሴት 249,902 ውስጥ 88.4% አልፈዋል። ​በዚሁ መሠረት ውጤት ለማየት ከዚህ በታች የቀረበውን ሊንክ በመክፈት፤ የመፈተኛ ቁጥርዎን (Registration Number) ማስገባት፤ ቀጥሎም የመጀመሪያ ስምዎን በማስገባት ውጤትዎን መመልከት ትችላላችሁ።👇 ​ሊንክ፦ https://oromia6.ministry.et