← All news
News Jul 30, 2026 · 40d ago

ኤችአይቪ በደማቸው ከሚገኙ ሰዎች መካከል 36 በመቶው የሚሆኑት ሴቶች ናቸው

‎ ‎አሁን ላይ በአገራችን ከፍተኛ የሆነ የኮንዶም ዕጥረት መኖሩም ተነስቷል። ‎ ‎ዕድሜያቸው ከ14-24 የሆኑ ሴቶች በተለይ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ለኤችአይቪ በከፍተኛ ሁኔታ የተጋለጡ መሆናቸው ተገልጿል። ‎ ‎በአገራችን ከግማሽ ሚሊየን በላይ ሰዎች ቫይረሱ በደማቸው ውስጥ ይገኛል ተብሏል። ‎ ‎አሁን ላይ 7መቶ ሺህ ሰዎች ቫይረሱ በደማቸው ውስጥ ይገኛል የተባለ ሲሆን፥ቁጥሩ ግን በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መሆኑን ሰምተናል። ‎ይህን የሰማነው የኔትወርክ ኦፍ ኔትወርክስ ኦፍ ኤች.አይ.ቪ ፖዘቲቭስ ኢን ኢትዮጵያ(ኔፕ ፕላስ) ይህን አስመልክቶ በሰጠው መግለጫ ነው። ‎ ‎ኔፕ ፕላስ በኤችአይቪ ህመም ዙሪያ ትኩረቱን አድርጎ የሚሰራ ተቋም ሲሆን፥ ምስረታው ወደ 22 ዓመት እየተጠጋው ነው። ‎ ‎በዚህ ኔትወርክ ስር የተቋቋሙ ከ5መቶ በላይ ማህበራትን የያዘ መሆኑ ሲገለፅ፥ በዋናነት አሁን ላይ በንቃት የሚንቀሳቀሱት እና የግሎባል ፈንድ ተጠቃሚ ማህበራት ቁጥር 1መቶ29 ነው። ‎ ‎የኔትወርክ ኦፍ ኔትወርክስ ኦፍ ኤች.አይ.ቪ ፖዘቲቭስ ኢን ኢትዮጵያ(ኔፕ ፕላስ) ዋና ዳይሬክተር አቶ ካሳሁን ታደሰ፥ በሚቀጥለው ወር 21ኛ ጠቅላላ ጉባዔ እንደሚካሄድ አስታውቀዋል። ‎ ‎ይህ ጉባዔ እየተዘነጋ ስላለው ነገርግን ዛሬም የብዙዎችን ህይወት እየቀጠፈ ስላለው የኤችአይቪ ህመም ሰፊ ግንዛቤ የሚሰጥበት ነው። ‎ ‎ድርጅቱ ለሁለት ጊዜ ያህል "Stigma index research" ማሰራቱን ገልጾ፥ ሶስተኛ ዙር ጥናት እያካሄደ መሆኑን አስታውቋል። ‎በጉባኤው ላይ የጤና ሚኒስቴር ሀላፊዎች ፣ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት፣ ከሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች፣ ከኔፕ ፕላስ ማህበራት የተወከሉ በአጠቃላይ 1መቶ20 እንግዶች ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል። ‎ ‎@Seledadotio