← All news
News Jul 30, 2026 · 40d ago

ግብጾች የአባይን ውሃ ስለሚጠቀሙ ለኢትዮጵያ ሊከፍሉን ይገባል ዶክተር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር

የውኃና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ሀብታሙ ኢተፋ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ባደረጉት ልዩ ቆይታ፣ ግብፅ የአባይን ውኃ በነፃ እየተጠቀመች አገሯን እያለማች በመሆኗ ለኢትዮጵያ ተገቢውን ክፍያ ልትፈጽም እንደሚገባ ገለጹ። ሚኒስትሩ በቆይታቸው እንደጠቆሙት፤ ኢትዮጵያ የጎርፍ አደጋ በታችኞቹ የተፋሰሱ አገራት—በተለይም በግብፅ ላይ እንዳይደርስ ከፍተኛ የክትትልና የእንክብካቤ ሥራ እያከናወነች ትገኛለች። ሆኖም አገራቱ የኢትዮጵያን የተፈጥሮ ሀብት ያለምንም ክፍያ በመጠቀም አገራቸውን እያለሙ በመሆናቸው፣ ለሚጠቀሙበት ውኃ ለኢትዮጵያ ክፍያ ሊፈጽሙ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።