ደቡብ ኮሪያ ዜጎቿ ትዳር እንዲመሠርቱእና ልጅ እንዲወልዱ ገንዘብ እየከፈለች እንደሆነ ተነገረ።
በዓለማችን ዝቅተኛው የወሊድ መጠን የሚገኝባት ደቡብ ኮሪያ፣ የህዝብ ቁጥሯ እንዳይቀንስና የህጻናት ቁጥር እንዲጨምር ትልቅ አዲስ ዘመቻ ጀምራለች! መንግሥት ወጣቶች እንዲጋቡና ልጅ እንዲወልዱ የሚያበረታቱ የገንዘብ፣ የቤት እና የህጻናት ማደጊያ ድጋፍ ፕሮግራሞችን ይፋ አድርጓል። ወዲያው ጋብቻ የሚፈፅሙ አዲስ ባለትዳሮች 1ኛ የመኖሪያ ቤት ድጋፍ፣ 2ኛ የህጻናት ማደጊያ አበል፣ 3ኛ የወሊድ ክፍያ እና የአካባቢ አስተዳደሮች የሚሰጧቸውን ልዩ ልዩ ማበረታቻዎች በአንድ ላይ ሲደመሩ አጠቃላይ የሚያገኙት ድጋፍ ከፍተኛ መጠን ሊደርስ ይችላል። ኢትዮጵያ ውስጥ ተመሳሳይ የጋብቻና የወሊድ የገንዘብ ማበረታቻ ቢጀመር... እርስዎ ያገባሉ?