92 ሚሊዮን የሚጠጋ የኢትዮጵያ ሕዝብ "ጤናማ የምግብ ሥርዓት" ለመከተል አቅም እንደሌለው የተመድ የምግብ ዋስትና ሪፖርት አመለከተ።
በኢትዮጵያ ጤናማ የምግብ ሥርዓትን ለማስጠበቅ በነፍስ ወከፍ የሚወጣው ወጪ ከምሥራቅ አፍሪካ ከፍተኛው መኾኑን ሪፖርቱ ጠቅሷል። ባለፈው የአውሮፓዊያን ዓመት የኢትዮጵያ የነፍስ ወከፍ ጤናማ የምግብ ወጪ 4 ነጥብ 7 ዶላር እንደነበርና ይህም ከኬንያ፣ ኡጋንዳና ታንዛኒያ የበለጠ መሆኑን ሪፖርቱ አመልክቷል። ከአውሮፓዊያኑ 2023 እስከ 2025 60 በመቶ ኢትዮጵያዊያን "መካከለኛ" እና "ከፍተኛ" የምግብ ዋስትና እጦት ገጥሟቸው እንደነበርም ሪፖርቱ ጠቅሷል። ሪፖርቱ የትግራይ ክልልን መረጃ አላካተተም።