8 ኢትዮጵያውያን 160 ኪሎ ግራም ጫት ወደ ሳውዲ አረቢያ ሊያስገቡ ሲሉ በቁጥጥር ስር ዋሉ።
በሳውዲ አረቢያ የጸጥታ አካላት ባካሄዷቸው የፍተሻ እና የቁጥጥር ስራዎች፣ የድንበር ህግ የተላለፉ 8 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ማዋላቸው ተገለጠ። በጃዛን ክልል አል-ዳየር (Al-Daer) በተባለው ቀጠና የሚንቀሳቀሱ የድንበር ጠባቂ የፓትሮል አባላት 160 ኪሎ ግራም ጫት ይዘው ሲንቀሳቀሱ ያገኟቸውን 8 የኢትዮጵያ ዜጎች በቁጥጥር ስር ማዋላቸው ተዘግቧል። Via Saudi Gazette እባካችሁን ወጣቶች ህይወታችሁን እና የወደፊት ተስፋችሁን አደጋ ላይ የሚጥሉ ድርጊቶች ላይ ከመሰማራት ተቆጠቡ! ጉርሻ page