← All news
News Jul 26, 2026 · 44d ago

ባለሥልጣናቱ መታሰራቸው ተሰማ‼️

በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የ ELMIS(የኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓት)  ፕሮጀክት ኃላፊ እና የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ዋና ሥራ ፈጻሚን ጨምሮ በርካታ ከፍተኛ አመራሮች በፌደራል ፖሊስ በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ተሰምቷል። ተጠርጣሪዎቹ በውጭ ሀገር ሥራ ስምሪትና በ ELMIS ሲስተም መረጃ በማጥፋት፣ በከባድ ሙስና፣ በሕገ-ወጥ የሰው ዝውውር እና የመንግሥትን የውጭ ምንዛሬ ለግል ጥቅም በማዋል ወንጀሎች የተጠረጠሩ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ በከፍተኛ የምርመራ ሂደት ላይ እንደሚገኝ የዘገበው ዘሀበሻ ነው።