← All news
News Jul 26, 2026 · 44d ago

በደቡብ ወሎ ገዳም በተፈጸመው ጥቃት ፓትርያርኩ ተጠያቂዎች ለፍትሕ እንዲቀርቡ ጠየቁ

​ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ በደቡብ ወሎ ሀገረ ስብከት በቦረና ወረዳ በግዮን አባይ ገዳም ላይ ሐምሌ 15 ቀን 2018 ዓ.ም. በተፈጸመው ጥቃት ጥብቅ መግለጫ አወጡ። ​በጥቃቱ የመነኮሳይያት ሕይወት ማለፉን፣ በርካቶች መቁሰላቸውንና በንዋየ ቅድሳቱ ላይ ውድመት መድረሱን የገለጹት ቅዱስነታቸው፣ በዚሁ ዕለት በሀድያና ስልጤ ሀገረ ስብከት የአምልኮ ሥፍራ መፍረሱንና በምእመናን ላይ ጥቃት መድረሱን አውግዘዋል። ​መንፈሳዊ ማዕከላት የሰላምና የእሴት ምንጭ በመሆናቸው፣ ገዳማትን መጠበቅ የባለሥልጣናትና የሕግ አስከባሪዎች ኃላፊነት መሆኑን አስገንዝበዋል። አሰቃቂውን ድርጊት የፈጸሙ አካላት በአስቸኳይ ለፍትሕ እንዲቀርቡ፣ ለሌሎች ገዳማት ጥበቃ እንዲደረግና ለተጎዱት ድጋፍ እንዲያገኝ ጥሪ አቅርበዋል። ​በመጨረሻም ሕዝበ ክርስቲያኑ ከተጎዱት ጎን እንዲቆም አሳስበው፣ ለተበደሉት ፍትሕንና ለሀገሪቱ ሰላምን ተመኝተዋል።