← All news
News Jul 24, 2026 · 46d ago

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በዲጂታል ገንዘቦች እና በቨርቹዋል ሀብቶች ዝውውር ላይ ጥብቅ እገዳ ጣለ

​የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በህግ ከተፈቀደው ውጪ በማናቸውም የቨርቹዋል ሀብቶች ግብይት ማድረግ በጥብቅ የተከለከለ መሆኑን አስታወቀ። ​እገዳው ቢትኮይንን ጨምሮ ሌሎች ክሪፕቶከረንሲዎችን ብቻ ሳይሆን፣ ለማንኛውም ክፍያና ኢንቨስትመንት የሚያገለግሉ በዲጂታል መልኩ የሚተላለፉ መግለጫዎችንም ያካትታል። ​በተለይም የሚከተሉት ተግባራት ሙሉ በሙሉ የተከለከሉ ናቸው ብሏል ባንኩ; 👉በቨርቹዋል ሀብት እና በመደበኛ ገንዘብ መካከል የሚደረግ መመንዘር 👉​በቨርቹዋል ሀብቶች መካከል የሚደረግ ልውውጥና ዝውውር 👉​የቨርቹዋል ሀብቶችን ማስቀመጥ፣ ማስተዳደር እና የፋይናንስ አገልግሎት መስጠት ​ህብረተሰቡ ከህጋዊ ተጠያቂነት፣ ከማጭበርበር፣ ከሳይበር ጥቃት እና ከከባድ የገንዘብ ኪሳራ ለመጠበቅ ከነዚህ እንቅስቃሴዎች እንዲቆጠብ ባንኩ አሳስቧል።