← All news
News Jul 23, 2026 · 47d ago

ለምክክር ጉባዔ መጥታ ወንድ ልጅ የተገላገለችው እናት የልጇን ሥም "ኮሚሽን" አለችዉ

ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ተወክላ በሀገራዊ ምክክር ጉባዔ ላይ እየተሳተፈች የምትገኘው ወ/ሮ ሀዳ አልማህዲ ወንድ ልጅ በሰላም የተገላገለች ሲሆን ስሙንም "ኮሚሽን" ብላዋለች። ባሳለፍነው ሳምንት በሀገራዊ ምክክሩ ላይ በመሳተፍ ላይ የነበረች የጋምቤላ ክልል ተወካይዋ ወ/ሮ ክርኑዶ ኡጁሉ ወንድ ልጅ በሰላም ተገላግላ ስሙም "ምክክር" መባሉ የሚታወስ ነው። ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ኡራ ወረዳ የመጣችው ሌላኛዋ የምክክሩ ተሳታፊ ወ/ሮ ሀዳ አልማህዲ በተመሳሳይ ወንድ ልጅ በሰላም የተገላገለች ሲሆን፥ ስሙንም "ኮሚሽን" ብላዋለች። የመውለጃ ጊዜዬ እየደረሰ መሆኑን ባውቅም ለኢትዮጵያዊያን አብሮነትና ለሀገራችን ዘላቂ ሰላም በጋራ በሚመከርበት በዚህ ጉባኤ መሳተፍ አለብኝ በሚል አቋም ተገኝቻለሁ ብላለች፡፡ በጉባኤው አጀንዳዎች ላይ ለሀገራችን ይበጃል የምትለውን ሀሳብ በመስጠት ንቁ ተሳትፎ ስታደርግ የቆየች ሲሆን፥ በዚህ ታሪካዊ ወቅት ልጇን በመገላገሏ መደሰቷን ገልጻለች። ዘገባዉ የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሚዲያ ነዉ።