መረጃ‼️
59 በመቶው የኢትዮጵያ ሕዝብ በአንድ ክፍል ቤት ውስጥ እንደሚኖር የፌደራል ስታትስቲክስ አገልግሎት ከአውሮፓዊያኑ 2024 እስከ 2025 ያካሄደው ጥናት አመለከተ። የመኖሪያ ቤቶች መጨናነቅ በተለይ በከተሞች አካባቢ እንዲባባስ ካደረጉት ምክንያቶች አንዱ፣ ከገጠር ወደ ከተማ የሚደረገው ያልተቋረጠ ፍልሠት መኾኑን ዋዜማ ከጥናቱ ላይ ተመልክታለች። በተጠቀሠው ጊዜ ውስጥ በጥናቱ 31 በመቶ የሴቶች እና 24 በመቶ የወንዶች ፍልሠት ተመዝግቧል። የተሻለ የሥራ ዕድል፣ ትምህርትና የመሠረተ ልማት አቅርቦትን ፍለጋ የሚደረገው ፍልሠት፣ በከተሞች ላይ የመኖሪያ ቤት አቅርቦት ላይ ከፍተኛ ጫና በመፍጠሩ በባለ ሁለት ክፍል ቤቶች የሚኖሩ ዜጎች ድርሻ 31 በመቶ መድረሱን ሪፖርቱ ያትቷል።