← All news
News Jul 22, 2026 · 48d ago

የድሮን ጥቃት‼️

በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ “በመካነ ሰላም ቅድስት አርሴማ አንድነት ገዳም በድሮን ጥቃት የመነኮሳት ህይወት አለፈ”‼️ በዛሬው ዕለት ሐምሌ 15/2018 ዓ.ም በምዕራብ ወሎ በመካነ ሰላም በዓባይ ወንዝ ዳርቻ በሚገኘው ዓባይ ገዳመ አስቀጤስ የሰማእቷ ቅድስት አርሴማ አንድነት ገዳም ተብሎ በሚጠራው ቦታ ላይ በተፈፀመ የድሮን ጥቃት ምክንያት በገዳሙ ውስጥ የሚኖሩ 2 ሴቶች ወዲያው ህይወታቸው ማለፉን እና ሌሎች መቁሰላቸውን ምንጮች ገልጸዋል። ጥቃቱ የተፈፀመው በአካባቢው የፋኖ ሀይሎች ከትመዋል በሚል ነው ተብሏል። ሰላም ለሀገራችን🕊🕊