← All news
News Jul 22, 2026 · 48d ago

ጄኤፍኤም 106.7 ሬድዮ ሞገድ ለስድስት ወራት ታገደ!

የመገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን በጄኤፍኤም 106.7 ሬድዮ ጣቢያ ላይ የስድስት ወራት የስርጭት እግድ ጣለ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን የጄኤፍኤም (JFM 106.7) ሬድዮ ጣቢያ የብሮድካስት ስርጭት ከሐምሌ 1/2018 ዓ.ም ጀምሮ ለሚቀጥሉት ስድስት ወራት ሙሉ ለሙሉ እንዲታገድ መወሰኑን አስታወቀ። ባለሥልጣኑ ውሳኔውን ያስ አስተላለፈው ጣቢያው በተደጋጋሚ የተሰጡትን የቃልና የጽሁፍ ማስጠንቀቂያዎች ሳይቀበል በመቅረቱ እና በአዋጅ ቁጥር 1238/2013 የተጣሉበትን የፈቃድ ውል ግዴታዎች ባለመወጣቱ እንደሆነ ገልጿል። ባለሥልጣኑ ባደረገው የይዘት ክትትልና የአካል ኢንስፔክሽን ምልከታ ጣቢያው በህግ የተጣለበትን የሀገራዊ ይዘት ሽፋን አለማካተቱን፣ ህዝብን የሚያስተምሩና የሚያዝናኑ ፕሮግራሞችን ከማቅረብ መቆጠቡን እንዲሁም ለሀገራዊ እሴቶችና ለፖለቲካዊ-ኢኮኖሚያዊ እድገት አስተዋጽኦ የማድረግ ግዴታውን አለመወጣቱን አረጋግጧል። በውሳኔው መሰረት የኢትዮጵያ ኮሚዩኒኬሽን ባለሥልጣንም ጣቢያው የተመደበለትን 106.7 የሬድዮ ሞገድ በእግዱ ወቅት እንዳይጠቀም ማሳሰቢያ የሰጠ ሲሆን፣ ጣቢያው ለሕግ ተገዢ በመሆን ስርጭቱን በአስቸኳይ እንዲያቆም ታዟል።